በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ክስ በሌለበት ሁኔታ ፍርድ አይኖርም- የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር አቶ ይልቃል ጌትነት


ፋይል ፎቶ - የሰማያዊ ፓርቲ ደጋፊዎች በአዲስ አባባ ሰልፍ ወጥተው ባለበት ወቅት የተነሳ እ.አ.አ. 2015
ፋይል ፎቶ - የሰማያዊ ፓርቲ ደጋፊዎች በአዲስ አባባ ሰልፍ ወጥተው ባለበት ወቅት የተነሳ እ.አ.አ. 2015

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር አቶ ይልቃል ጌትነት

ሊቀ መንበሩ አቶ ይልቃል ጌትነትና አንድ ሌላ ከፍተኛ አመራር እንዲሰናበቱ የጠየቀው የሰማያዊ ፓርቲ የሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ውሳኔ፤ በፓርቲው የኦዲትና ቁጥጥር ኮምሽን እየታየ ነው።

የኮምሽኑ ሊቀ መንበር አቶ አበራ ገብሩ ለአሜሪካ ድምጽ እንዳስረዱት አቶ ይልቃል ከፍተኛ ቅሬታ፤ ሌላ አንድ የአመራር አባል ደግሞ አቤቱታ አቅርበዋል።

የብሔራዊ የሥነ ምግባር ኮሚቴው ሠብሳቢ ወ/ሮ ሃና ዋለለኝ እንዳሉት በአቶ ይልቃልና በሌሎች አራት የአመራር አባላት ላይ የቀረበው ክስ የታየው በኮሚቴው መመሪያና በፓርቲው መተዳደሪያ መሠረት ነው።

የሰማያዊ ፓርቲ የሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ውሳኔ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:24 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የሰማያዊ ፓርቲ አርማ
የሰማያዊ ፓርቲ አርማ

ክስ በሌለበት ሁኔታ ፍርድ አይኖርም :- የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር አቶ ይልቃል ጌትነት

ክስ በሌለበት ሁኔታ ፍርድ አይኖርም ያሉት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር አቶ ይልቃል ጌትነት በብሔራዊ የስነ-ምግባር ኮሚቴው የተወሰነባቸው የማሰናበት ውሳኔ ህገ-ወጥ ነው ብለዋል።

የሰነ-ሰርአት ኮሚቴውና ኮሚቴውን ያቋቋመው የኦዲትና የቁጥጥር ኮሚሽንም ስራየን እንዳልሰራ ሃላፊነትንም እንዳልወጣ አድርገውኛል ያሉት አቶ ይልቃል ጠቅላላ ጉባኤ መጥራተቸውንም አስታውቀዋል። የተፈጠረው ችግር ሊፈታ የሚችለውም በጠቅላላ ጉባኤ ነው ብለዋል።

ዘጋብያችን እስክንድር ፍሬው አቶ ይልቃልን አነጋግሮ ከአዲስ አበባ የላከው ዘገባ አለ፣ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

ክስ በሌለበት ሁኔታ ፍርድ አይኖርም- የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር አቶ ይልቃል ጌትነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:42 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG