በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“አውዳሚ የምላቸውን ሐሳቦች ለመፋለም ሞክሬያለሁ”በዕውቀቱ ስዩም


በዕውቀቱ ስዩም
በዕውቀቱ ስዩም

ደራሲ እና ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም “ባለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት የሚጻፉ አንዳንድ መጽሐፎች በሕብረተሰብ መካከል፣ በተለይ በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል ያለውን ትስስር የሚያላሉ፣አልፎ አልፎ ደግሞ እንዲበጠስ የሚያግዙ አስተያየቶችን እና ሐሳቦችን አያለሁ፡፡”ይላል፡፡

ወጣቱ ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም “ከዐሜን ባሻገር” የተሰኘ መጽሐፉን እሁድ ጥር 22 ቀን 2008 ዓ.ም በሐዋርድ ዩኒቨርስቲ ብላክ በርን ሴንተር አስመርቋል። ከምርቃት ዝግጁቱ በኋላ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጠው ቃለምልልስ፤ ስለመጽሐፉ ርእስ ስያሜ ተጥይቆ፤ "አሜን ብለን ስንቀበላቸው የቆየናቸው የታሪክ፣ አልፎ አልፎም የፖለቲካ አስተያየቶች፣ ስለ አኗኗራችን በተቋሞች፣በትምሕርት ቤት፣ በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ወይም ደግሞ መንግሥታዊ ባልሆኑ በተለያዩ ተቋሞች አማካኝነት የሚቀርቡልንን የተዛቡ አስተያየቶች ተደጋግመው ስለተነገሩ ብቻ “አሜን” ብለን የተቀበልናችውን አስተያየቶች የሚሞግቱ መጣጥፎችን ለመጻፍ ነው የሞከርኩት፡፡ በዛ ምክንያት ነው “ከዐሜን ባሻገር”ያልኩት" ብሏል፡፡

አያይዞም፤ "አሜን ብለን ከምንቀበላቸው እውነታ ባሻገር ያለው ምን ይመስላል? የሚለውን ለማሳየት የሞከርኩት፡፡ እነዚህን ሐሳቦች ልንሞግታቸው ይገባል፡፡ ምክንያቱም አብሮ መኖራችንን ይሸረሽሩታል፡፡ ለሕልውናችን አስጊ ናቸው፡፡ ብዬ አስባለሁ፡፡ ስለዚህ እነሱን የሚሞግቱ ነገሮችን ለመጻፍ ሞክሬያለሁ፡፡ አውዳሚ የምላቸውን ሐሳቦች ለመፋለም ሞክሬያለሁ"ይላል፡፡

ጽዮን ግርማ አነጋግራዋለች፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

“አውዳሚ የምላቸውን ሐሳቦች ለመፋለም ሞክሬያለሁ”በዕውቀቱ ስዩም
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:22 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG