በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ራያ ቢራ ፋብሪካ ገበሬዎችን በመኖ እያገዘ ነው


ራያ ቢራ ፋብሪካ በማይጨው ከተማ አቅራቢያ ላሉ ገበሬዎች እስካሁን ከሦስት ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ተረፈ-ምርት በእርዳታ መስጠቱን አስታውቋል፡፡

በማይጨው ከተማ በአንድ ቢሊዮን ሰባት መቶ ሚሊዮን ቢሊዮን ብር መዋዕለ-ነዋይ የተቋቋመው የራያ ቢራ ፋብሪካ በደቡብ ትግራይ ያጋጠመውን የእንስሣት መኖ እጥረት ለመቋቋም የፋብሪካውን ተረፈ-ምርት ለገበሬዎች በነፃ እያከፋፈለ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፋብሪካው እስካሁን ሦስት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሺህ ብር የሚገመት እርዳታ የሰጠ ሲሆን በዚህ ዓመት ሃያ ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ተረፈ-ምርት ለገበሬዎቹ በነፃ ለመስጠት አቅዷል።

ግርማይ ገብሩ ገበሬዎቹን አነጋግሮ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይድምጡ።

ራያ ቢራ ፋብሪካ ገበሬዎችን በመኖ እያገዘ ነው /ርዝመት - 5ደ28ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:28 0:00

XS
SM
MD
LG