በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲስ የቲቢ መድኃኒት ሥራ ላይ ዋለ


የቲቢ ሕክምና እንክብሎች
የቲቢ ሕክምና እንክብሎች

ቤዴኩዊላይን በሙከራ ላይ የሚገኝ ባለፉት ሃምሣ ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ አዲስ መድኃኒት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ለሕክምና አገልግሎት እንዲውል የዩናይትድ ስቴትስ የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር ይሁንታ ቸሮታል፡፡




please wait

No media source currently available

0:00 0:08:04 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አዲስ የቲቢ መድኃኒት - ቤዴኩዊላይን
አዲስ የቲቢ መድኃኒት - ቤዴኩዊላይን

ቤዴኩዊላይን በሙከራ ላይ የሚገኝ ባለፉት ሃምሣ ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ አዲስ መድኃኒት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ለሕክምና አገልግሎት እንዲውል የዩናይትድ ስቴትስ የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር ይሁንታ ቸሮታል፡፡

እየሞቱ ያሉ የቲቢ ሕሙማን ጥናትና ፍተሻ እስኪያልቅ የመጠበቂያ ጊዜም፣ ትዕግሥትም የላቸውም፡፡ ወጣም ወረደ ፈዋሽ መድኃኒት ባለመኖሩ እየሞቱ ናቸውና፡፡

በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር በ2011 ዓ.ም በዓለም ዙሪያ ለትዩበርክዩለስስ (ለቲቢ) ከተጋለጠው ኤችአይቪ በደሙ ውስጥ የሚገኝ ወደ 1.1 ሚሊየን ሰው ሰባ ዘጠኝ ከመቶ የሚሆነው የሚገኘው ከሰሃራ በስተደቡብ ባለው የአፍሪካ ክፍል ነው፡፡ ይህም ከስምንት መቶ ሺህ በላይ የሚሆነው ማለት ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር ቤዴክዊላይን ሥራ ላይ እንዲውል የፈቀደው ካለፈው 2012 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ ነበር፡፡ ፍቃዱን ሲሰጥ ግን አብሮ ያሠፈረው ማሣሰቢያ “ከቲቢ ለመውጣት ሌላ አማራጭ ለሌላቸው ሕመምተኞች” ይላል፡፡

ቤዴክዊላይን ገና ሙሉ ዕውቅናና የፍቱንነት ማረጋገጫ አላገኘም፡፡ ገና ብዙ ሙከራዎችና ፈተናዎችንም ማለፍ ይጠበቅበታል፡፡

ይህ መድኃኒት እንደሌሎች ማንኛቸውም መድኃኒቶች ሁሉ ከሥጋትና ከተጓዳኝ አደጋ ወይም ሪስክ ነፃ አይደለም፡፡ ከእንዲህ ዓይነቶቹ ተጓዳኝ ችግሮች አንዱ የልብ ምት ሥርዓት መዛባት ይጠቀሣል፡፡

እንደማንኛቸውም ብርቱ መድኃኒቶች ዝርዝር ማስጠንቀቂያዎችም አብረውት ይወጣሉ፡፡ ደግሞም ለሁሉም ታካሚ ያለገደብ መፍትሔ እንደማይሆንም ይታወቃል፡፡

ሌላው ጥያቄ የዋጋ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ መድኃኒት ምን ያህል ወጭ እንደሚጠይቅ ገና በውል እንደማይታወቅ የጠቆሙት ዶ/ር ካክስ አምራቹ ኩባንያ በተቻለ መጠን ለሁሉም ታካሚ በቀላል ዋጋ እንዲገኝ ለማድረግ እንደሚሠራ ማረጋገጫ መስጠቱን አመልክተዋል፡፡

የቲቢ መድኃኒቶች በአጠቃላይ ውድ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ለተጨማሪ የዘገባውን ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG