ዋሽንግተን ዲሲ —
ባንግላዴሽ ውስጥ የሚገኘው ትልቁ የእሥልምና ፓርቲ መሪ በጦር ወንጀለኛነት የተላለፈባቸውን የሞት ፍርድ፣ የሃገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ረቡዕ እንዳፀናው ተገለጸ።
አክራሪውን ጃማአት ኤ ኢስላሚ ፓርቲ ይመሩ የነበሩት የቀድሞ ካቢኔ አባል የነበሩት ሞቲዉር ራህማን ኒዛሚ ያቀረቡት ይግባኝ ውድቅ የተደረገው በአንድ የፍርዱ ሸንጎ ላይ በተሰየሙ የዳኞች ቡድን መሆኑም ታውቋል።
ኒዛሚ ባንግላዴሽ ከፓኪስታን ጋር እአአ በ1971 ባካሄደችው የነፃነት ውጊያ ወቅት የነበራቸውን ሥልጣን መከታ በማድለግ እንደፈፀሟቸው በተነገረ ጅምላ ግድያ፣ ወከባ፣ መድፈርና ንብረት ማውደም ወንጀሎች የተከሰሱት ባለፈው ዓመት ጥቅምት ውስጥ ነበር።
ለዘገባው የተያያዘውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።