በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመቀሌ የባጃጅ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች አደሙ


የመቀሌ ባጃጅ
የመቀሌ ባጃጅ

ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ አስተያየታቸውን የሰጡት የባጃጅ ባለቤቶች እንደሚገልፁት መመርያው የስራ ነፃነትን ይገድባል። ​​የስምሪት መለያ ለጥፈን በምንሰራበት ጊዜ የኮንትራት ስራ ብናገኝና ወደሌላ ቦታ ብንንቀሳቀስ የትራፊክ ፖሊስ ያለቦታችሁ ተገኝታቿል በሚል ቢቀጣን መመርያው አያስጥለንም ይላሉ።

በመቀሌ የሚገኙ ከ1500 በላይ የሚሆኑ የባጃጅ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች መንግሥት የስምሪት መለያ እንዲለጥፉ የሚያዘውን መመርያ በመቃወም ነው አድማውን የመቱት። ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ አስተያየታቸውን የሰጡት የባጃጅ ባለቤቶች እንደሚገልፁት መመርያው የስራ ነፃነትን ይገድባል።

ፋይል ፎቶ - መቀሌ ከተማ
ፋይል ፎቶ - መቀሌ ከተማ

የስምሪት መለያ ለጥፈን በምንሰራበት ጊዜ የኮንትራት ስራ ብናገኝና ወደሌላ ቦታ ብንንቀሳቀስ የትራፊክ ፖሊስ ያለቦታችሁ ተገኝታቿል በሚል ቢቀጣን መመርያው አያስጥለንም ይላሉ።

በዋነኝነት ደግሞ መመርያው ሳናምንበት በትእዛዝ እንድናተገብረው እያስገደዱን ነው በሚልም የከተማዋን የትራንስፖርት ጽሕፈት ቤትን ይከሳሉ።

የመቀሌ ዞን የኮንስትራክሽን፣ የመንገድና የትራንስፖርት ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ መሐሪ ገብረ ህይወት በበኩላቸው አደሙ የሚል መረጃ የለንም የሚል መግለጫ ሰጥተዋል።

ቢሆንም ግን የመንግሥትን መመርያ በመተግበር ሕብረተሰቡን እንድያገለግሉ እየሰራን ነው ይላሉ።

መመርያው በተደጋጋሚ ውይይት እንደተካሄደበት የገለፁት አቶ መሐሪ መመርያው የኮንትራት ስራ እንዳይሰሩ አያግድም ብሏል። የመመርያው ዋና ዓላማ በትራንስፖርት እጥረት የሚሰቃየውን ህዝብ ለመጥቀም የተዘጋጀ ነው ይላሉ ሐላፊው።

ከ1500 በላይ የሚሆኑ የመቀሌ ባጃጅ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች የመንግሥትን መመርያ በመቃወም አድማ መምታቸው ተሰማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:13 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG