በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮሎኝ ጀርመን ሴቶች ላይ ጥቃት ከደረሰ በኋላ፣ በአውሮፓ ያለው የኢሚግረሽን ቀውስ መልኩን ቀይሯል


በኮሎኝ ጀርመንና በሌሎችም ከተሞች በአውሮፓውያን አዲስ አመት ወቅት በሴቶች ላይ የደረሰውን ጥቃት ያስተባበሩት የስደተኞች ቡድኖች ናቸው ከተባለ በኋላ በአውሮፓ ያለው የኢሚግረሽን ቀውስ መልኩን ቀይሯል። የስዊድን ፖሊሶች ስዊድን ውስጥ በሴቶች ላይ የደረሰውን ተመሳሳይ ጥቃት ሸፋፍነዋል ለሚለው ክስ የሀገሪቱ ባለስልጣኖች መልስ መስጠት ይኖርባቸዋል።

PEGIDA የተባለው የጀርመን ቀኝ ክንፍ ቡድን ያስተባብበረው ጸረ ስደተኞች ሰልፍ በሚካሄድበት በአበሁኑ ወቅት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች መቻቻል እንዲኖር ጥሪ በማድረግ ሌፕዚግ በተባለችው ምስራቃዊት ከተማ መንገዶች ላይ ሰልፍ ወጥተዋል። ጸረ ስደተኞች ቡድኖች በምዕራቡ አለም እስላማዊነትን ማስፋፍት የሚሉትን በመቃወም ስልፍ ማደረግ ከጀመሩ ውልለው ውድረዋል።

ታትያና ፌስቴሪንግ የተባለች የPEGIDA መሪ ሰደተኞቹ ሴቶችን ማጥቃት ጀመረዋል ትላለች።

“እነዚህ ሙስሊም ስደተኞች አጠቃላይ የሽብር ጥቃት ጀምረዋል። የጀርመን ሴቶችን፣ ነጣ ያለ የደጉር ቀለም ያላቸውን ነጭ ጀርመናውያን ሴቶችን እያጠቁ ነው።” End Act.

ጸረ ስደተኞች የሆኑ ቡድኖች ትላንት ኮሎኝ ከተማ ላይ በፓኪስታን፣ በሶርያና በአፍሪቃውያን ሰደተኛ ወንዶች ላይ ተከታታይ ጥቃቶች አካሂደዋል።

ይሁንና በርካታ የሃገሪቱ ሴቶች ጥቃቱን ለመቃወም በመንገዶች ወጥተዋል። የጽንፈኛዎቹ ቀኞች ተቃዋሚ የሆነው የኮሎኝ ቡድን አባል የሆነችው Emily Michels PEGIDA የተባለው ጽንፈኛ ቡድን ተግባር እንደሚያስቆጣት ገልጻለች።

“PEGIDA በአሁኑ ወቅት የሚፈጽመው ተግባር ያስቆጣኛል። PEGIDAም ሆነ በዛሬ እለት የተሰባሰቡት ዱርየዎች ሁሉ ስለሴቶች መብት ደንታ እንደሌላቸው ሁላችንም የምናውቀው ነገር ነው። ሁሌም ቢሆን እዚህ የሚመጡት የውጭ ሀገራት ተወላጆችን ለመደብደብ ነው። ፕሮፓጋንዳቸውን ለማሰማት እንጂ በሴቶች ላይ የሚፈጸመውን መድልዎ ለመቃወም አይወጡም።”

በሌላ ዜና ደግሞ ስዊድን ውስጥ ፖሊሶች በአዲሱ አመት በአል ወቅት አብዛኛውን ጥቃት የፈጸሙት ስደተኞች ናቸው የሚለውን ወሬ ሸፋፍነዋል እያሉ ነው የሃገሪቱ ሚድያ ዘገባዎች። የብሄራዊው ፖሊስ ሀላፊ ዳን ኤልያሰን በክሱ ላይ ምርመራ እንደሚካሄድ ትላንት አስታውቀዋል።

“ይህ ጉዳይ በሚገባ መጣራት ያለበት ነገር ነው። ይህ ዜና እውነትነት ካለው መስተካከል ይኖርበታል። ያጠፋ ሰው ካለ ማጣራት ይኖርብናል።”

የጀርመን ቻንስለር አንጌላ መርከል ደግሞ ገደብ የሌለው የሰደተኞች ፍልሰት ጋብ እንዲል ያስፈልጋል ብለዋል።

“ለሰዎች መሰደደ ምክንያት የሆኑትን ነገሮች መዋጋቱ ላይ ማትኮር ይኖርብናል። አሁን በተጀመረው አዲስ አመት ውስጥ ማድረግ የምንፈልገው ነገር የስደተኞችን መጠን ጉልህ በሆነ መንገድ እንዲቀንስ ማድረግ ነው። እዚህ ያሉት ስደተኞች ከህዝቡ ጋር እንዲወሃዱ ማድረግ ስለሚያስፈልግ በአሁኑ ወቅት ሰዉ ሁሉ የሚነጋገርበት ነጥብ ሰደተኞቹን ለማወሀድ የተሻለው መንገድ የትኛው ነው የሚለው ነው? ባለፈው ሌሊት ላይ የተፈጸመውን አስከፊ ድርጊት ስለምናውቅ የመዋሃድ ተግባርን ለማሳካት በህብረተሰቡ ዘንድ ግልጽነት እንዲኖር ያስፈልጋል። ይሁንና ስደተኞቹም የኛን ህግና እሴትን ለማክበር ፍላጎት እንዲኖራቸው ያስፈልጋል።”

በግጭትና በበትርምስ ባህል ላደጉት አንዳንድ ሰዎች ከህዝቡ ጋር የመዋሃዱ ጉዳይ ከባድ ሊሆንባቸው ይችላል።

አደተኞች ከሰሜን ምስራቅ፣ ከመካከለኛው ምስራቅና ከአንዳንድ የእስያ ልፍሎች ወደ አውሮፓ በሚጎርፉባት በአሁኑ ወቅት የአውሮፓ መንግስታት ስደተኞቹን ባስታናገዱት ሀገሮች የተከሰተውን ጸረ ስደተኞች ስሜት ለማርገብ እየታገሉ እንደሆነ በመግለጽ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ Zlatika Hoke ያጠናቀረችውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ አቅርባዋለች።

በኮሎኝ ጀርመን ሴቶች ላይ ጥቃት ከደረሰ መኋላ በአውሮፓ ያለው የኢሚግረሽን ቀውስ መልኩን ቀይሯል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:18 0:00

XS
SM
MD
LG