በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሽብርተኝነት ተጠርጥረዉ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ከመደበኛ የሥራ ቀናት ዉጪ ፍርድ ቤት መቅረባቸዉ ተገለጸ


ከሃያ ስምንት ቀናት በፊት የፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት፣ አቶ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዱዓለም አራጌ አቶ ዘመኑ ሞላ፣ አቶ ናትናኤል መኮንንና አቶ አሳምነዉ ብርሃኑ ፍርድ ቤት በቀረቡበት መስከረም 3 ቀን 2004 ዓም፥ ፍርድ ቤቱ ለሁሉም የሰጣቸዉ ተለዋጭ ቀጠሮ፣ ለጥቅምት 2 2004 ዓም 8 ሰዓት እንዲቀርቡ ነበር። ይሁንና ይህ የፍርድ ቤት ቀጠሮ በእለቱ እንዳልተካሄደ ነገር ግን የታሳሪዎቹ ችሎት በዝግ ከስራ ሰዓት ዉጪና የአንዳንዶቹም በእሁድ እንደተካሄደ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።


ዝግ ችሎቱ የታሳሪዎቹን ሁኔታ ለመከታተል ብቻ ሳይሆን ጠበቃ እንዳይቆምላቸዉ እድል እየነፈገ ነዉ ይህም ከፍለ ያለ የሰብአዊ መብት ጥሰት ነዉ ብለዋል።

XS
SM
MD
LG