በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብና የሰሜን ሱዳን ስምምነት ሲተነተን


የካርቱም መንግስት በአጨቃጫቂዋ የAbyei ግዛት ያሰማራውን ኃይል ሙሉ በሙሉ ሊያወጣና በምትኩም የኢትዮጵያ የሰላም ጠባቂ ሠራዊት ወደ አካባቢው እንዲሰማራ ከደቡብ ሱዳን አስተዳደር ጋር በትላንትናው ዕለት አዲስ አበባ ውስጥ መስማማታቸው ይፋ ተደርጓል።

የደቡብ ሱዳን ነፃ አገርነት ሊታወጅ በሳምንታት የሚቆጠር ጊዜ ብቻ በቀረው ባሁኑ ወቅት፥ በሁለቱ ወገኖች መካከል ዳግም ጦርነት እንዳይቀሰስ ሥጋት ፈጥረው ከቆዩት በርካታ ደንቃራዎች መካከል ዋነኛው ይሄው በነዳጅ ሃብቷ የበለፀገችው የAbyei ጉዳይ መሆኑም ይታወቃል።

በካርቱምና በጁባ መካከል የተደረሰውን የዚህን አዲስ ስምምነት ይዘት፥ አንድምታና በሁለቱ አገሮች ቀጣይ ዕጣም ሆነ በንዑስ አህጉሩ ዘላቂ ሰላም ላይ ሊኖረው በሚችለው ሚና ዙሪያ በአካባቢው ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ጥናት ያደረጉ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ለትንታኔ ጋብዘናን አወያይተናል።

ዝርዝሩን ከዚህ ያድምጡ፤

XS
SM
MD
LG