በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዴሞክራሲያዊ እሴቶች በዓለም ሕዝቦች ዘንድ ተቀባይነት አላቸዉ


በአረቡ ዓለም የተቀሰቀሱት ሕዝባዊ ንቅናቄዎች ዴሞክራሲያዊ እሴቶች በዓለም ሕዝቦች ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው እንደሆኑ ማሣየታቸው ተገለፀ፡፡የተደራጀ ወንጀል ለዴሞክራሲ አደጋን እየጋረጠ ነውም ተብሏል፡፡

ትላንት ረቡእ በአፍሪቃ ህብረት ዋና ጽህፈት ቤት የተከፈተዉ ሁለተኛዉ የአፍሪቃ ህብረትና የአሜሪካ መንግስታት ድርጅት የጋራ ጉባኤ ሁለቱ አህጉራዊ ድርጅቶች በዴሞክራሲና ሰብአዊ መብቶች ላይ ባዘጋጁት ስብሰባ ስለዴሞክራሲ እሴቶችና የተጋረጡባቸዉ ችግሮች ተወያይተዋል።

በስብሰባዉ ላይ ንግግር ያደረጉት የዓለም አቀፍ ተቋም የዴሞክራሲና የምርጫ ድጋፍ ዋና ጸሃፊ ቪደር ሄርግሰን፣ ባሁኑ ዘመን ዴሞክራሲ ያለዉን የማደግ እድልና የተጋረጠበትንም አደጋ በግልጽ አስቀምጠዋል። በህዝብ የተመሩ የሰሜን አፍሪቃ ንቅናቄዎች ዴሞክራሲያዊ እሴቶች የዓለም ህዝቦች ሁሉ የሚጋሩዋቸዉ ለመሆናቸዉ መልካም ምሳሌ እንደሆኑ ጠቅሰዉ። ሰላማዊ በሆነ መንገድ ዴሞክራሲያዊ ለዉጦችን ለሚያስገኙ ለእኩልነትና ለተስተካከ የፖለቲካ ጥቅሞት ዜጎች በጋራ መታገል እንደሚችሉ ተናግረዋል። ሆኖም ድንበር ዘለል የተደራጁ ወንጀሎች ገና ዴሞክራሲን በመገንባት ላይ ላሉ አገሮች ብቻ ሳይሆን የተደላደለ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ገንብተዉ ለሚገኙም አደጋ እንደሆኑ አስገንዝበዋል።

የአፍሪቃ ህብረት አቻ የሆነዉ የአሜሪካ መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ሆዜ ሚጉዌል ኤል ሱልዛ በበኩላቸዉ ፣ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር እንዳይለመለም እንቅፋት የሚሆኑ የአደንዛዥ እዕ አዘዋዋሪ ወንጀለኞችና፣ ለተቋሞች ፈተና የሚጋርጡ የድህነት ሁኔታዎች ናቸዉ ብለዋል።
ሙሉ ዘገባዉን ከመለስካቸዉ አመሃ ያዳምጡ።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG