በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፀረ-ኤድስ የገንዘብ ድጋፍ መቀነስ በአዲስ አበባው የኢካሳ ጉባዔ አቢይ ትኩረት እንደነበር ተገለጠ


በዓለም ላይ ለፀረ-ኤድስ እንቅስቃሴዎች የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ መቀነስ ዛሬ ማምሻውን በአዲስ አበባ በተጠናቀቀው ጉባዔ ጎልቶ የወጣ አጀንዳ እንደነበር የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አስታወቁ።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በተለይ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በጉባዔው ላይ ከአሥር ሺህ በላይ ተሣታፊዎች መገኘታቸውንና የተሣካም እንደነበር ገልጠዋል።

ሚኒስትሩን ያነጋገራቸው እስክንድር ፍሬው ተከታዩን ዘገባ ከአዲስ አበባ አስተላልፏል።

XS
SM
MD
LG