በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እርዳታ በአርሲም እየታደለ ነው


በምእራብ አርሲ ሻላ ወረዳ አጄ ከተማ ለአካባቢው ነዋሪዎች የእህል እርዳታ ታደለ፡፡

የዝናቡ አመጣጥ ለተከታታይ ዓመታት ባለመስተካከሉ ለድርቅ መጋለጣቸውን የአካባቢው አርሶ አደሮች ይናገራሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት ከለጋሾች የተገኘውን እህል ለጉዳተኞቹ እያደለ ነው።

ምዕራብ አርሲ ሻላ ወረዳ ማዕከል በሆነችው አጄ ከተማ ዙሪያ ካሉ ቀበሌ ማህበራት የሸሹ የድርቅ ተጠቂዎች የአስቸኳይ እርዳታ እህል ተሰጥቷቸዋል። እርዳታው የተገኘው ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ እርዳታ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) እና ከካቶሊክ የእርዳታ ድርጅት ሲሆን አስቸኳይ የምግብ እደላ ፕሮግራሙን የሚያካሄደው የኢትዮጵያ መንግሥት ነዉ።

የእርዳታዎቹም ዓይነቶች የታሸጉ ጥራጥሪዎችና የቆርቆሮ ዘይት መሆኑን ሪፖርተራችን እስክንድር ፍሬው ዘግቧል።

እርዳታ ሲቀበሉ ካነጋገራቸው አርብቶ አደሮች አንዱ አቶ ሼካቶ ቀሹር የችግሩ መንስዔ የዝናብ መጥፋት መሆኑን ተናግረዋል።

"ዝናብ በመጥፋቱ ሣር ደረቀ፤ መኖ ሲጠፋ ከብቶቻችንም አለቁ፤ ከብቶቻችንን ሸጠን እህል መሸመትም አልቻልንም፤ ማምረትም አልቻልንም፡፡ ረሃብ ያጠቃን ስለዚህ ነው ብለዋል። አርሶ አደሩ ቀድሞ ሃያ ስምንት ከብቶች የነበሯቸው ሲሆን ዛሬ ሁለት ብቻ እንደቀሯቸው ተናግረዋል።

ሙሉውን ዘገባ ከእስክንድር ፍሬው ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG