በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስር ላይ የሚገኙትን አራት የኦፌኮ አመራር አባላት መጠየቅ እንዳልቻሉ ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ


የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡበት ወቅት የተነሳ ፎቶ [ፋይል - ሮይተርስ]
የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡበት ወቅት የተነሳ ፎቶ [ፋይል - ሮይተርስ]

“ጠዋት ቂሊንጦ ስንሄድ አራቱ ሰዎች የሉም። ያሉበትን የሚነግረን አላገኘንም።” ወ/ሮ ዓይናለም ደበሎ፤ ላለፉት አራት ወራት በማዕከላዊ እሥር ቤት የነበሩትና ካለፈው አርብ አንስቶ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተዛውረዋል፤ ከተባሉት የኦሮሞ ፌድራሊስት አመራር አባላት ቤተሰብ አባላት አንዷ ናቸው።

በኦሮምያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ከተካሂዱት የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ተዛምዶ እሥር ቤት የሚገኙት አራት የኦሮሞ ፌድራሊስት አመራር አባላት አንስቶ መጠየቅ ያለመቻላቸውን ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ።

የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ (የኦፌኮ) አርማ
የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ (የኦፌኮ) አርማ

ላለፉት አራት ወራት በሚገኙበት የማዕከላዊ እሥር ቤት እየተመላለሱ ሲጠይቋቸው የነበሩት የአቶ ጉርሜሳ አያኖ፥ የአቶ አዲሱ ቡልቡላ፥ የአቶ ደጀኔ ጣፋና የአቶ በቀለ ገርባ የቤተሰብ አባላት ናቸው፤ አራቱ ታሳሪዎች ካለፈው አርብ አንስቶ ከአዲስ አበባ ከተማ ወጣ ብሎ ወደሚገኘው የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተዛውረዋል፥ ቢባሉም፤ ይዘውላቸው የሄዱትን ስንቅ ለማቀበልም ሆነ ሊጠይቋቸው ያለመቻላቸውን ለአሜሪካ ድምጽ የገለጹት።

እስር ላይ የሚገኙትን አራት የኦፌኮ አመራር አባላት መጠየቅ እንዳልቻሉ ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:14 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG