በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአረና መሪ ብርሃኑ በርኸ ተፈቱ

አቶ ብርሃኑ በርኸ - የአረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉዓላዊነት መሪ
አቶ ብርሃኑ በርኸ - የአረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉዓላዊነት መሪ

መቀሌ ላይ ለሁለት ቀናት ታስረው የነበሩት የተቃውሚው አረና ትግራይ መሪ ዛሬ ረቡዕ ጥር 20/2007 ዓ.ም ተፈትተዋል፡፡

የአረና ትግራይ አርማ
የአረና ትግራይ አርማ

መቀሌ ላይ ለሁለት ቀናት ታስረው የነበሩት የተቃውሚው አረና ትግራይ መሪ ዛሬ ረቡዕ ጥር 20/2007 ዓ.ም ተፈትተዋል፡፡

የአረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉዓላዊነት ሊቀመንበር አቶ ብርሃኑ በርኸ ከከትናንት በስተያ ሰኞ ጥር 18/2007 ዓ.ም የታሠሩት ወንጀል ተፈፅሞበታል ተብሎ በሚጠረጠር ቤት ውስጥ በመገኘታቸው፣ በወንጀል አድራጎት ትብብርና “ፖሊስ ተሣድበሃል” በሚሉ ምክንያቶች እንደነበር የፓርቲው የቀድሞ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አሥራት ትናንት - ማክሰኞ ለቪኦኤ በስልክ ገልፀው ነበር፡፡

አቶ ብርሃኑ በርኸ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “የታሠርኩት በፖለቲካ ማዋከብ ነው፤ የተፈታሁትም በፖለቲካ ነው” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG