በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጅምላ አስመጭዎች አሰራራቸውን ካላሻሻሉ መንግስት በቀጥታ አስመጥቶ ሊያከፋፍል ተዘጋጅቷል


መንግስት በችርቻሮ ሱቆች የጠፉ እንደ ስኳር መሰል አላቂ እቃዎችን በኮታ ማከፋፈል ጀምሯል
መንግስት በችርቻሮ ሱቆች የጠፉ እንደ ስኳር መሰል አላቂ እቃዎችን በኮታ ማከፋፈል ጀምሯል

“ይሄ ደርግ ያደርግ እንደነበረው እራሳችን ገብተን እንቸረችራለን ነው የሚሉት፤ የበለጠ ችግር ያመጣል” ፕሮፌሰር ሰይድ ሀሰን

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር መንግስት በንግዱ ዘርፍ ላይ የጠበቀ ቁጥጥር እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርላም ንግግር በሰፊው ያተኮረው በኑሮ ውድነት ላይ ነው። በተጨባጭ የአንዳንድ ሸቀጦቹን ዋጋ ጣራ መንግስት ያወጣ ሲሆን፤ በመንግስቱ መመሪያ ገበያው በፍላጎትና አቅርቦት አለመመጣጠን ደርሶበት ሱቆች ባዷቸውን ነው የከረሙት።

አቶ መለስ በዚህ ንግግራቸው መንግስታቸው የዋጋ ንረትን ለመቀነስ እየወሰዳቸው ያሉትን የማክሮ ኢኮኖሚ (የአጠቃላይ ምጣኔ ሀብት) እርምጃዎች በዝርዝር አስረድተዋል።

በተለይ መንግስታቸው በአጠቃላይ ምጣኔ ሀብቱ የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር በበጀት፤ በገንዘብና በውጭ ምንዛሬ የወሰዳቸውን እርምጃዎች በሰፊው ተንትነዋል።

በመስከረም ወር የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ምንዛሬ ማስተካከያ አድርጓል። ይሄ እርምጃ የዋጋ ንረትን እንዳያባብስ፤ ግሽበቱ እስኪቀንስ ጠብቆ መንግስት በውጭ ምንዛሬ ክምችቱ ተከስቶ የነበረውን እጥረት ለመቀነስ እርምጃ መውሰዱን ነው አቶ መለስ የተናገሩት።

ፕሮፌሰር ሰይድ ሀሰን በመሪ ስቴይት ዪኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር ናቸው። አቶ መለስ በፓርላማ ያቀረቡት ሪፖርት መንግስት በአጠቃላይ ኢኮኖሚው ያለውንና የሚኖረውን ጣልቃ ገብነት፤ ብሎም የጠበቀ ቁጥጥር የጠቆመ ነው ይላሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዋጋ ንረትን ለመታደግ፤ የጅምላ አስመጭዎች ጋር መንግስታቸው አብሮ እንደሚሰራ፤ ሁኔታውን ለጥቂት ወራት አጢኖ፤ ለውጥ የማይመጣ ከሆነ መንግስትና የመንግስት ድርጅቶች ከውጭ በገፍ ቁሳቁሶችን ሸምተው እንደሚያከፋፍሉ መግለጻቸው የሚያሳየው ነገር ቢኖር ይላሉ ፕሮፌሰር ሰይድ፤ አንደኛ የአቅርቦት እጥረት መኖሩንና ሁለናኛው ደግሞ በደርግ ስርዓት ይደረግ እንደነበረው በኮታ መካፋፈል መጀመሩን ነው።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG