በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ ካለፈው ምርጫ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እሁድ ዕለት መቀሌ ከተማ ውስጥ ሕዝባዊ ስብሰባ አካሄደ


የድርጅቱ መሪዎች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ዘርዘር ያለ መግለጫ ሰጡ

የመድረክ አመራር አባላት በስብሰባው ላይ ሲናገሩ፥ የኢትዮጵያ መንግሥት እየወሰዳቸው ያለውን አንዳንድ እርምጃዎች የሚስማሙባቸውና የማይቀበሏቸውም እንዳሉ ለያይተው አስቀምጠዋል። የወቅቱ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አሥራት መድረክ ከኤርትራ ጋር ያለውን ግንኙነት በሰላማዊና በሕጋዊ መንገድ መፈታት አለበት ብሎ ያምናል ብለዋል።

አቶ ገብሩ በዓባይ ወንዝ ላይ ይገነባል ስለተባለው የሚለንየም ግድብም አንስተው፥ ድርጅታቸው የዓባይ ወንዝ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ጥቅም ማስከበር አለበት ብሎ እንደሚያምንና መሠራቱን ፈጽሞ እንደማይቃወም አስረድተው፥ በቂ ጥንቃቄ መወሰድ እንዳለበት ግን አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ባዘጋጀው የአምስቱ ዓመት የትራንስፎርሜሽንና የልማት እቅድ ላይም አስተያየት የሰጡት የወቅቱ የመድረክ ሊቀ መንበር በተለይ መሬት ለውጭ ባለሃብቶች በገፍ የመሰጠቱን ጉዳይ እንጠይቃለን ብለዋል።

ኢትዮጵያ በሙስና የምትታወቅ ሀገር ሆናለችናም አስቸኳይ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ሲሉም አቶ ገብሩ አሥራት መክረዋል።

ዝርዝሩን ከዚህ ያድምጡ

XS
SM
MD
LG