በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግስት እጁን ከሃይማኖት ተቋማት ላይ እንዲያነሳ መኢአድ ጠየቀ


በሙስሊሞችና ክርስቲያኖች ላይ የኢትዮጵያ መንግስት አደረሰው የሚለውን ጥቃት መኢአድ አውግዟል

የመላ ኢትዮጵያ ሕዝብ ድርጅት ዛሬ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ በሃይማኖት ተቋማት ላይ በመንግስት በደል እየደረሰ ነዉ ብሏል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በእስልምናና በክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ እየተወሰደ ያለዉ የሃይል እርምጃ ኢህአዴግ ለህገ መንግሥታዊ መብት ያለዉን ንቀት ያሳያል ብሏል።

የመኢአድ መግለጫ ሰሞኑን በመንግስት ጸጥታ ሃይሎችና በሙስሊም ማሃበረሰብ አባላት መካከል የተከሰተዉን ግጭት መነሻ ያደረገ ሲሆን፣ መንግሥት ግጭቱን ያነሳሱት “የሃይማኖት ጭምብል ያጠለቁ አክራሪዎች” ናቸዉ ይላል።

መኢአድ ግን የአክራሪነትና የአሸባሪነት አዝማሚያዎች በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዉስጥ መኖር ያለመኖራቸዉ ከኢሃዴግ ዉጪ በማንም አልተረጋገጠም፣ የመብት ጥያቄ ያነሳ ሁሉ በኢሃዴግ እይታ አሸባሪ ነዉ ይላል።

መኢአድ በሃይማኖት ተቋም ዙሪያ ሌላ ያነሳዉ በዋልድባ ገዳም ባካባቢዉ ባለ የስክዋር ፕሮጄክት ምክንያት ይደርሳል ያለዉን ጉዳት ነዉ። መንግስት በገዳሙ ዙሪያ የያዘዉ የልማት አጀንዳ የሃይማኖቱን ተከታዮች እየጎዳ ነዉ ብሎአል በመግለጫዉ ።

በተጨማሪም የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የጤንነት ችግር አስመልክቶ ምክትላቸዉ ተክተዉ አለመስራታቸዉ የህግ መንግቱን ሙሉነት ጭምር ጥያቄ ምልክት ዉስ ያሰገባ ነዉ ብለዋል የመኢአድ አመራር አባላት በሰጡት መግለጫ። ዝርዝሩን ከእስክንድር ፍሬዉ ዘገባ ያድምጡ

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG