በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የካሉብና ሂላላ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችትን በጥቅም ላይ ለማዋል የወጣው ጨረታ በቅርቡ ይፋ ይደረጋል


የቻይና ኩባያ ጨረታውን አሸንፏል የሚሉ ዘገባዎችን የማእድን ምንስቴር አስተባብሏል

በሶማሊ ክልል የሚገኘውን የካሉብ የተፈጥሮ ጋዝ የነዳጅ ክምችት በግል ኩባንያዎች እንዲበለጽግ የማእድን ምንስቴር ያወጣውን ጨረታ ከሶስት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

አንዳንድ የጋዜጣ ዘገባዎች የጨረታው አሸናፊ የቻይና ኩባንያ እንደሆነ ጠቁመዋል። እንደዘገባዎቹ በ200 ሚሊዮን ዶላር የካሉብና ሂላላ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችትን ለማበልጸግ መሰረቱን በሆንግ ኮንግ ያደረገ የቻይና ኩባንያ ተጫርቷል።

የማእድን ሚኒስትር ወይዘሮ ስንቅነሽ እጂጉ የጨረታው አሸናፊ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ ይፋ እንደሚሆን ገልጸው፤ ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ የፍለጋና የማበልጸግ ሃላፊነቱ የሚሰጠው ድርጅት አይታወቅም ብለዋል።

ከወይዘሮ ስንቅነሽ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG