በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ተሽመድምደዋል ሲል አምነስቲ አሳሰበ


በኢትዮጵያ በተግባር ላይ የዋለው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ለመመዝገብና ለማስተዳደር የወጣው አዋጅ፤ የሰብዓዊ መብት ስራዎችን አከርካሪ ሰብሯል ይላል፤ የመብት ተሟጋች ቡድኑ አምነስቲ ኢንተርናሽናል።

ድርጅቱ በዚህ ሳምንት ይፋ ባደረገው አዲስ የሁኔታ አጣሪ ዘገባ፤ በኢትዮጵያ የሴቶች፣ የህጻናት፣ የቡድንና የግለሰብ መብት ዙሪያ የሚሰሩ ድርጅቶች፤ አገልግሎቶቻቸውን እንዲዘጉና እንዲገድቡ ተገደዋል ይላል።

ከሶስት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ በተግባር ላይ የዋለው የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ለመመዝገብና ለማስተዳደር የወጣው አዋጅ፤ በአገሪቱ የሰብዓዊ መብት ስራዎች አስተጓጉሏል፤ አልፎም አንዳንድ ድርጅቶች ስራቸውን እንዲያቋርጡ አድርጓል ይላል የአምነስቲ ኢንተርናሽናል አዲስ ሪፖርት።

“በጣም በርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ስማቸውንና ስራቸውን ለመቀየር ተገደዋል። ስራቸውን “ልማታዊ” ተብሎ በተቀየሰላቸው መንገድ ብቻ እንዲያተኩሩ ሆነዋል” ይላሉ የአምነስቲ የአፍሪካ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ሚሸል ጋጋሪ። “በሰብዓዊ መብት ስራቸው ለመቀጠል ያሰቡ ጥቂት ድርጅቶች፤ የገንዘብ ድጋፍ ስለማያገኙ አገልግሎቶቻቸውን እያቆሙ ነው።”

ካጋሪ አክለውም በዚህ ጥናት ላይ በቅርበት ክትትል የተደረገባቸው ሁለት ትላልቅ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በባንክ የሚገኘው ገንዘባቸው እንዳይንቀሳቀስ ታግዷል፤ ስራቸውም ከዚህ ቀደም ከነበረው 10 ከመቶ የማይሞላ ነው ይላሉ።

በ1987ዓ.ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በአንድ ወቅት ከ17ሽህ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊ ሴቶች ነጻ የህግ ምክርና ድጋፍ ይሰጥ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ማህበሩ ለስራው ያገኘው የነበረው የገንዘብ ድጋፍ በመንጠፉ፤ ስራውን በበጎ ፈቃድ አገልጋዮች ወስኖ የተመጠነ አገልግሎት ለመስጠት ተገዷል።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናሏ ሚሸል ካጋሪ የኢትዮጵያ መንግስት ይሄንን ህግ ከማውጣቱ በፊት፤ በግለሰብና በቡድን ማለትም የሴቶች መብት፣ የህጻናት ጉዳይ፣ የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ የአራጋዊያንና ሌሎች የማህበረሰቡ አካላትን ይዞታ ለማሻሻል በሚሰሩ ድርጅቶች ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽዕኖ ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በህብረት አስታውቆ እንደነበር ያወሳሉ።

የኢትዮጵያ መንግስት ግን በህገ-መንግስቱ የተረጋገጠውን የዜጎች የመደራጀት መብት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ሕግ ውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ለአገሪቱ ዜጎች የሚሰጡትን ሚና የሚያሳልጥ ህግ ማውጣት አስፈላጊ መሆኑን በህጉ መድቅም አስቀምጦ በፓርላማ አጽድቆታል።

XS
SM
MD
LG