በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለማየሁ ሩባያት፤ ሃይኩ፤ እና ግራፊቲ


«ሩባያት፥» «ሃይኩ፥» እና «ግራፊቲ» የተሠኙ ሶስት የግጥም መድብሎች ለንባብ አብቅቷል።

የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ የግጥም ዘይቤዎች፤ ሶስተኛው ግን ማንነቱ ያልታወቀ ሠው በተለያዩ ቦታዎች ተፅፎ የሚገኝ ፅሁፍ መጠሪያ ነው፤ ገጣሚው የሶስተኛው መፅሃፉ ርዕስ ሊያደርገው የመረጠው።

ዓለማየሁ ታዬ ይባላል። ለበርካታ ዓመታት በራዲዮና በህትመት ጋዜጠኝነትም ሠርቷል። በግጥም ሥራዎቹ፥ ህይወትና ስነ ፅሁፍ ዙሪያ ከአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ባህልና ማኅበረሰብ ፕሮግራም ጋር የተወያየው ዓለማየሁ፤ የኦማር ኻያም ሩባያትና፥ እንዲሁም ሃይኩ የተባለው በተፈጥሮ ላይ የሚያጠነጥነው የግጥም አፃፃፍ ዘይቤዎች በኢትዮጵያም በሥፋት ይለመዱና ይዘወተራሉ፤ የሚል ተስፋ እንዳለው ይናገራል።

XS
SM
MD
LG