በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመድብለ ፓርቲ ዕጣ በኢትዮጵያ


«የአንድ ፓርቲ በተቀባይነት ጎልቶ መውጣት ወይስ የአንድ ፓርቲ ብቸኛ ሁሉን አድራጊነት?» በግራና ቀኝ የሚሰሙ የሁለት ወገን የክርክር ጭብጦች ናቸው።

የገዢውን የኢህአዴግ ፓርቲን በመደገፍና በመቃወም በሁለት ጎራ የተሠለፉ ተከራካሪዎች፥ «መድብለ ፓርቲ፤» በኢትዮጵያ ያለውን ዕጣ አስመልክቶ እሰጥ አገባ ገጥመዋል።

የግንቦቱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ውጤት ተከትሎ፥ በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከምርጫው በኋላ ዛሬ ያላቸው ድርሻና ሊጫወቱ የሚችሉት ቀጣይ ሚና በአንድ ወገን፤ የምርጫውን ውጤት ሙሉ ሊባል በሚችል ድምፅ የወሰደው ገዢው ኢህአዴግ ቢያንስ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት አገሪቱ የምትጓዝበትን አቅጣጫ በሁሉም መልኩ የመወሰን ሥልጣን፤ ያለው ብቃትና ችሎታ፤ እንዲሁም የሚከተለው የፖለቲካ መስመር ለሁለት ወገኑ ክርክር መነሻ ሆነው ቀርበዋል።

የእሰጥ አገባ ተከራካሪዎች በሁለት ተቃራኒ ጫፎች የቆሙ ይመስላሉ። ያድምጧቸው።


XS
SM
MD
LG