በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ውይይት፥ «ቡና የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት፥ ባህልና ልማት!» ክፍል ሁለት፤


ቡና፥ ባህል፥ የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት መብት (Intellectual Property Rights) እና ልማት ምን ያገናቸው ይሆን?

በቦስተን ዩኒቨርሲቲ የፍሬዴሪክ ፓርዲ የጥናት ማዕከል ለህትመት በበቃውና የኢትዮጵያን ምርጥ ቡና የንግድ ምልክት ባለቤትነት ያረጋገጠውን ጥረት በምሳሌነት የተመለከተን አንድ ጥናት መነሻ በማድረግ የተጀመረ ውይይት ነው።

አንድ የምርት ውጤት ቁሳዊ ይዞታው ከሚያስገኛቸው ቀጥተኛ ጠቀሜታዎች ባሻገር ሊገኙ የሚችሉትንና intangible values በመባል የሚታወቁትን፤ የምርቱን ልዩ ይዘት፥ ምንነት፥ ሥምና ዝና አለያም ዕውቅና፤ እንዲሁም ምርቱ የፈለቀበትን ባህል የመሳሰሉ ባህሪያት ጨምሮ በአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት መብት (Intellectual Property Rights) ውስጥ የሚኖራቸውን ሚና ይመረምራል።

«ቡና፥ ባህልና የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት፤» የጥናቱ ባለቤት በሆኑት ዶ/ር ሄራን ሰረቀብርሃንና በቡና ጉዳዮች በሚፅፏቸው ፅሁፎች የሚታወቁት አቶ ወንድ ወሰን መዝለቂያ በርዕሱ ዙሪያ የጀመሩትን ውይይት ሁለተኛ ክፍል ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG