በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስላማዊ መንግሥት ጽንፈኛ ቡድን አባል የሆነ አሜሪካዊ በሰሜን ኢራቅ እጁን ሰጠ


የመሃመድ ጀማል ክዊስ(Mohamed Jamal Khweis)የአሜሪካ መንጃ ፈቃድ
የመሃመድ ጀማል ክዊስ(Mohamed Jamal Khweis)የአሜሪካ መንጃ ፈቃድ

አባቱ ፍልስጤማዊ እናቱ ደግሞ ከሞሱል ኢራቅ ናቸው ማለቱን ሳርባዝ ሃማ አሚን የተባሉ በኢራቅ የኩርዶች ፕሽመርጋ አዛዥ ጠቁመዋል። የቱርክ ገንዘብና ጥቂት ዶላር ይዞ ነበር። ቪዛ የገንዘብ ማውጫ ካርድና የአሜሪካ መንጃ ፈቃድ እንዳለው ወታደራዊው አዛዥ ተናግረዋል።

እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ጽንፈኛ ቡድን አባል የሆነ አሜሪካዊ በሰሜን ኢራቅ ለኩርድ ፕሽመርጋ ሃይሎች እጁን ሰጥቷል።

ሳርባዝ ሃማ አሚን (Sarbaz Hama-Amin) የተባሉ በኢራቅ የኩርዶች ፕሽመርጋ አዛዥ ሀይሎቻቸው ተጠርጣሪውን ያስታዋሉት ዛሬ ጥበቃ ላይ ሳሉ እንደሆነ ገልጸዋል። ሃይሎቹ አንድን ነገር ካስተዋሉ በኋላ መከታተል ጀመሩና ተሰወረ። ከዛ ሊነጋጋ ሲል ብርሃን ሆነና ሰውየው ጩኸት አሰማ።

"ወደናንተ መምጣት እፈልጋለሁና ማነው ሊያናግረኝ የሚችለው አለ በእንግሊዘኛ። ሃይሎቻችን እንግሊዘኛ ስለማይናገሩ እሱ በሚያውቀው ትንሽ አረብኛ እንግሊዘኛ የሚናገር ሰው ካለ ጠየቀና ፐሽመርጋዎቹ ፈንጂ እንዳልያዘ ካረጋገጡ በኋላ ታስሮ ወደ ሰፈር እንደተወሰደ እጁን መስጣት እንደሚፈልግ ተናገር” ሲሉ ወታደራዊው አዛዥ ገልጸዋል።

አባቱ ፍልስጤማዊ እናቱ ደግሞ ከሞሱል ኢራቅ ናቸው ማለቱን እሚን ጠቁመዋል። የቱርክ ገንዘብና ጥቂት ዶላር ይዞ ነበር። ቪዛ የገንዘብ ማውጫ ካርድና የአሜሪካ መንጃ ፈቃድ እንዳለው ወታደራዊው አዛዥ ተናግረዋል።

የኢራቅ ካርታ
የኢራቅ ካርታ

XS
SM
MD
LG