በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አል-ሻባብ ኬንያ ውስጥ 147 ተማሪ ገደለ


Kenya University Attack
Kenya University Attack

የአል-ሻባብ ታጣቂዎች በሰሜን ምሥራቅ ኬንያ ሶማሊያ ድንበር ላይ በሚገኘው ጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ ላይ ዛሬ ጠዋት አደጋ ጥለው 147 ተማሪዎችን መግደላቸውን የኬንያ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር፤ ጆዜፍ ንካዪሴሪ አስታወቁ፡፡

Kenya University Attack
Kenya University Attack

የአል-ሻባብ ታጣቂዎች በሰሜን ምሥራቅ ኬንያ ሶማሊያ ድንበር ላይ በሚገኘው ጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ ላይ ዛሬ ጠዋት አደጋ ጥለው 147 ተማሪዎችን መግደላቸውን የኬንያ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር፤ ጆዜፍ ንካዪሴሪ አስታወቁ፡፡

ከዋና ከተማይቱ ናይሮቢ በስተምሥራቅ 370 ኪሎሜትር ላይ በሚገኘው ጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ ላይ ጥቃቱ ከተፈፀመ በኋላ 160 ተማሪዎች ያሉበት እስካሁን እንደማይታወቅ ተነግሯል፡፡

አንድ የአል-ሻባብ ቃል አቀባይ ለሮይተርስ የዜና አውታር ደውሎ ቡድናቸው ብዙ ሰው በታጋችነት መያዙን አስታውቋል፡፡

ሰባ ዘጠኝ ተማሪዎች መቁሰላቸው ተገልጿል፡፡

የሃገር ውስጥ ጉዳይ መ/ቤቱ በትዊተር ገፁ ላይ ባወጣው መረጃ ከጥቃት አድራሾቹ ሁለት መገደላቸውንና የተያዙትን የማስለቀቅ ጥረቱ እንደቀጠለ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ጥቃቱ ከተጀመረ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ያሳወቀው የሶማሊያው የሽብር ቡድን አል-ሻባብ አደጋውን የጣለው ኬንያ ሶማሊያ ውስጥ ጦሯን በማሠማራቷ ለመበቀል እንደሆነ ገልጿል፡፡

Kenya University Attack
Kenya University Attack

ፖሊስ በሰጠው መግለጫ ታጣቂዎቹ የዩኒቨርሲቲውን ግቢ ሰብረው ከገቡ በኋላ ያለልዩነት መደዳውን መተኮስ እንደጀመሩ አመልክቷል፡፡

ከጥቃት አድራሾቹ አንዱ የሆነ አህመድ ካኖ የሚባል አል-ሻባብ ኬንያ ውስጥ ለሚያደርሣቸው ጥቃቶች የቡድኑ የውጭ ጉዳዮች መሪ ሽሽት ላይ መሆኑን የኬንያ ባለሥልጣናት ጠቁመው ሰዉ በንቃት እንዲጠብቅ ጠይቀዋል፡፡

በሌሎች ስሞችም ዱልያዳዪን ወይም ጋማዴሬ እየተባለ የሚጠራው ካኖ ዜግነቱ ኬንያዊ የሆነና በአውሮፓዊያኑ 1990ዎቹ ዓመታት እዚያው ጋሪሳ ውስጥ በሚገኝ የሃይማኖት ትምህርት ቤት የተማረ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ኡሁሩ ኬንያታ፤ የኬንያ ፕሬዚዳንት /ፎቶ ፋይል/
ኡሁሩ ኬንያታ፤ የኬንያ ፕሬዚዳንት /ፎቶ ፋይል/

ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በቴሌቪዥን ቀርበው ባደረጉት ንግግር ፖሊስና የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ለጥቃቱ ምላሽ የሚሰጡባቸውን ሁኔታዎች እያስተባበሩ መሆናቸውን አስታውቀው ሕዝቡም እንዲተባበር ጠይቀዋል፡፡

“በጉዳዩ ላይ እየሠራን ነን፤ ኬንያዊያን እንድትረጋጉ እጠይቃለሁ፡፡ ለፀጥታችንም ሥጋት ነው ከምትሉት እንቅስቃሴ ጋር ግንኙነት ያለው የሚመስላችሁን ማንኛውንም መረጃ ለባለሥልጣናቱ እንድትሰጡም እጠይቃለሁ” ብለዋል ፕሬዚዳንት ኬንያታ፡፡

ይህንን አስከፊ ያሉትን የሽብር ጥቃት ዩናይትድ ስቴትስ በብርቱ እንደምታወግዝና ሽብርተኝነትን ለማጥፋት ሃገራቸው ከኬንያ መንግሥትና ሕዝብ ጋር ትከሻ ለትከሻ እንደምትቆም በኬንያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሣደር ራበርት ጋዴክ አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG