በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤድስ ጉባዔ በኀዘንና በከፍተኛ ተስፋ ተከፈተ

የሜልቦርን የኤድስ ጉባዔ ሲከፈት በአይሮፕላን አደጋ ሳይደርሱ ለቀሩት ስድስት የኤድስ ተመራማሪዎችና ኤክስፐርቶች ተሣታፊዎች አዝነዋል
የሜልቦርን የኤድስ ጉባዔ ሲከፈት በአይሮፕላን አደጋ ሳይደርሱ ለቀሩት ስድስት የኤድስ ተመራማሪዎችና ኤክስፐርቶች ተሣታፊዎች አዝነዋል

ሃያኛው የዓለም የኤድስ ጉባዔ ትናንት፣ ዕሁድ - ሐምሌ 13/2006 ዓ.ም ሲከፈት ግዙፍ የተባሉ ግቦችን አስቀምጧል፡፡

ሃያኛው ዓለምአቀፍ የኤድስ ጉባዔ - ባነር
ሃያኛው ዓለምአቀፍ የኤድስ ጉባዔ - ባነር

please wait

No media source currently available

0:00 0:07:39 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ሃያኛው የዓለም የኤድስ ጉባዔ ትናንት፣ ዕሁድ - ሐምሌ 13/2006 ዓ.ም ሲከፈት ግዙፍ የተባሉ ግቦችን አስቀምጧል፡፡ አንዱም እጅግ የገዘፈ መድረሻ በመጭዎቹ 15 ዓመታት ውስጥ ኤችአይቪን ከገፀ-ምድር ማጥፋት ነው፡፡

የሜልቦርን የኤድስ ጉባዔ ሲከፈት በአይሮፕላን አደጋ ሳይደርሱ ለቀሩት ስድስት የኤድስ ተመራማሪዎችና ኤክስፐርቶች ተሣታፊዎች አዝነዋል
የሜልቦርን የኤድስ ጉባዔ ሲከፈት በአይሮፕላን አደጋ ሳይደርሱ ለቀሩት ስድስት የኤድስ ተመራማሪዎችና ኤክስፐርቶች ተሣታፊዎች አዝነዋል

ዓለምአቀፉ ጉባኤ ሜልቦርን - አውስትራሊያ ላይ ሲከፈት የበረታ የኀዘን ድባብ ሰፍኖበት ነበር፡፡ ባለፈው ሣምንት ውስጥ ለጉባዔው ለመድረስ ከሆላንድ ተነስተው ወደ ኳላ ለምፑር ሲጓዙ የነበሩ ስድስት ከፍተኛ ተመራማሪዎችና ኤክስፐርቶች ምሥራቅ ዩክሬን ውስጥ ከምድር በተተኮሰ የሚሳይል አረር ተመትቶ በወደቀው የማሌዥያ የመንገደኞች አይሮፕላን ውስጥ ነበሩ፡፡

ሜልቦርን በምሽት
ሜልቦርን በምሽት

እስከ ፊታችን ዐርብ በሚዘልቀው የዘንድሮው ጉባዔ ላይ አችአይቪን ለማምከንና መተላለፉን ለማስቆም፣ እንዲሁም ኤድስን ለማከምና ከእንግዲህ ማንም በኤድስ ምክንያት እንዳይሞት፣ ማንም ሕፃን ሲወለድ ከኤችአይቪ ነፃ ሆኖ እንዲወለድ ለማድረግ የተያዙትን የሣይንስ ጥረቶች፣ ኤችአይቪ በዓለም ዙሪያ ቤተሰቦችንና ማኅበረሰቦችን እንዴት እንደጎዳ እንደሆነና ና እየጎዳ ስላለባቸው ሁኔታዎተ ሰፋፊ ፍተሻዎችና ጥልቀት ያላቸው ውይይቶች በየመድረኩ ይካሄዳሉ፡፡

ኤችአይቪ/ኤድስ ባለፉት ሰላሣ ዓመታት ውስጥ ወደ አርባ ሚሊየን የሚሆን ሰው በዓለም ዙሪያ ገድሏል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG