በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በአስር ዓመት ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ እገባለሁ አለች።


በአስር ዓመት ውስጥ መካከለኛ ገቢ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:14 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

እስካሁን ባሉት አመልካች ሁኔታዎች ከተሄደ ኢትዮጵያ በመጪው አስር ዓመታት ጊዜ ዉስጥ መካከለኛ ገቢ ያላት አገር የመሆን ግባቸው እንደሚሳካ የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ።

አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ በተከፈተዉ የአፍሪቃ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤቶች ስብሰባ ላይ ባደረጉት የመክፈኛ ንግግር ነው አገራቸው በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉ ነዳጅ አምራች ያልሆኑ አገሮች አንዷ መሆኗን የተናገሩት።

“ፖሊሲዎቻችንና ስታራቴጂዎቻችን ብቃትና ጥራታቸዉን አረጋግጠዋል። እናም አሁን ያሉትን አመልካቾች ከተከተልን፥ ኢትዮጵያ በመጪዎቹ አስር ዓመታት ጊዜ ዉስጥ መካከለኛ ገቢ ያላት አገር የመሆን ግባችንን እናሳካለን፤” ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ እምነታቸውን ገልጠዋል። የዛሬውን ጉባኤ ያዘጋጀዉ ከአርባ በላይ አገሮች ብሔራዊ ምክር ቤቶች አባል የሆኑበት የፓን አፍሪቃ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ሲሆን የአህጉራዊው ተቋም ስራ አስፈጻሚ ዲሬክተር ኢትዮጵያዊው አቶ ክቡር ገና ናቸዉ። አቶ ክቡር የዛሬው ስብሰባ ዓላማ በአፍሪቃ ስለሚቋቋሙ የንግድ ቀጠናዎች መረጃዎች ለመለዋወጥ ጭምር መሆኑን ይፋ አድርገዋል።
XS
SM
MD
LG