በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በጋዜጦች


አፍሪቃ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን ስለ አፍሪቃ ከተጻፉት የተወሰኑትን ጨምቆ ያቀርባል። ኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ ጠየቀች፣ ኢትዮጵያ ከሰሀራ በመለስ ካሉት የአፍሪቅ ሀገሮች የመጀመርያው የባቡር አገልግሎት ጀመረች፣ የአፍሪቃ ቀንድ የአየር ንብረት እየሞቀና እየደረቀ እንደሚሄድ ታወቀ፣ United States ወደ ካሜሩን ወታደሮች ለመላክ ወሰነች የሚሉትን ርእሶች ነው በዛሬው ዝግጅታችን የምንመለከተው።

abcnews የተባለው የአሜሪካ የዜና ስርጭት ቴሌቪዥን ድረ-ገጽ ኢትዮጵያ ውስጥ በቂ ዝናብ ባለመገኘቱ የምግብ እጥረት በመከሰቱ 8.2 ሚልዮን የሚሆን ህዝብን በምግብና በሌላ አስፈላጊ ነገሮች ለመርዳት የኢትዮጵያ መንግስት አለም አቀፍ ረድኤት እየጠየቀ መሆኑን ዘግቧል።

የሃገሪቱ መንግስት ዜጎቹን በምግብና በሌሎች አስፍላጊ አቅርቦቶች ለመርዳት $192 ሚልዮን ዶላር መድቧል። እስከ ታህሳ ወር ባለው ጊዜ ለሚያስፈልገው አቅርቦት $596 ሚልዮን ዶላር እርዳታ እየጠየቀ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ የድርቅ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚቴ ጸሀፊ አቶ ምትኩ ካሳ መናግራቸውን ድረ-ገጹ ጠቁሟል።

CNN ድርግሞ ኢትዮጵያ ከሰሀራ በመለስ ካሉት የአፍሪቃ ሀገሮች የመጀመርያውን የቀላል ባቡር መጓጓዣ አገኘች ሲል ዘግቧል። 4 ሚልዮን የሚሆን ህዝብ በሚኖርባት አዲስ አበባ ሰዉ በሚኒ ባሶች ነበር የሚዘዋወረው። በአሁኑ ወቅት ግን የቀላል ባቡር አገልግሎት በመጀመሩ ሰዎች ወደ ስራ የሚሄዱበት መንገድ ፈጽሞ እንዲለዋጥ ያደርጋል ይላል የ CNN ድር-ገጽ ዘገባ።

ኢትዮጵያና ቻይና ተባብረው የስሩት የቀላል ባቡር አገልግሎት $475 ሚልዮን ዶላር የሚፈጅ ሲሆን ከሰሀራ በመለስ ካሉት የአፍሪቃ ሃገሮች የመጀመርያው ነው።

ካለፉት 20 አመታት ወዲህ በሀገሪቱ አዎንታዊ የሆነ የኢኮኖሚ እድገት ሲታይ ቆይቷል” ሲሉ የኢትዮጵያ የባቡር ሀዲድ ኮርፐረሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ጌታቸው በትሩ ተናግረዋል። 60,000 የሚሆኑ ከአዲስ አበባ ወጣ ብለው የሚኖሩትን ሰዎች ወደ መሀል ከተማ መጥተው የሚሰሩበትን መንገድ ያቀልላቸዋል ማለት ነው። “ባንዲት ከሰሀራ በመለስ ባሉት ሀገሮች ከተማ እንዲህ አይነት አገልግሎት ይኖራል ብሎ ማሰብ አይቻልም ነበር” ሲሉ ዶክተር ጌታቸው መግለጻቸውን ድረ-ገጹ ጠቁሟል።

Scientific American የተባለው ሳይንስ ነክ ስለሆኑት ጉዳዩች የሚዘግብ ድረ-ገጽ በበኩሉ የአፍሪቃ ቀንድ ክፍል ካለፉት 2,000 አመታት ወዲህ ከነበረው በበለጠ ፍጥነት እየሞቀና እየደረቀ እንደሄደ አንድ አዲስ ዘገባ ማመልከቱን ጠቁሟል። ይህ ጥናትም የጋዝ ልቀት በአለም ደርጃ እየጨመረ ሲሄድ የአፍሪቃ ቀንድ እርጥበት እየጨመረ ይሄዳል የሚለውን የአለም የአየር ንብረት ሞዴልን ይጻረራል።

ኢትዮጵያን፣ ሶማላያን፣ ኤርትራን፣ ጂቡቲንና ሱዳንን የሚያካትተው ምስራቅ አፍሪቃ ግጭቶች፣ ድርቅና ረሃብ ሲፈራረቁበት እንደቆየ የሚታወቅ ነው። አሁን ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ የአየር ለውጥ የሚያስከትለው የሙቀትና የድርቅ አደጋ እያንዣበበበት እንደሆነ ዘገባው ያወሳል። ሌላ ተጨማሪ ርኣስም አለን ሙሉውን ቅንብር ያድምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:09:00 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG