በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰው በሎቹ የአፍሪካ መንገዶች


በዓለም ላይ በያመቱ ከአንድ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን በላይ ሰው በመኪና አደጋ ይሞታል።

በያመቱም ከሰላሳ እስከ ሃምሳ ሚሊዮን የሚሆኑ ጉዳት የሚደርስባቸው ሲሆን አብዛኞቹም የአካል ጉዳተኞች ሆነው ይቀራሉ።

በኢትዮጵያ በእግረኞች ላይ የሚደርሰው አደጋ መጠን መቀነሱ ተነግሯል፡፡

ረቡዕ ጥቅምት 29/2004 ዓ.ም በአዲስ አበባው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስብሰባ ማዕከል የተጀመረው የሁለት ቀናት ጉባዔ ዋና ዓላማ ከ2011 እስከ 2020 ባሉት ዓመታት ተግባራዊ የሚሆነውን የአፍሪካ የመንገድ ላይ ዕቅድ መመርመርና ማፅደቅ ነው፡፡

በስብሰባው ላይ ይፋ የተደረጉት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የመኪና ግጭት አደጋ የሰውን ሕይወት በመቅጠፍና ለአባል ጉዳት በመዳረግ በዓለም ላይ ግንባር ቀደም ከሚባሉት አንዱ ነው፡፡

በመላው ዓለም በየቀኑ በመኪና አደጋ ምክንያት 3 ሺህ 300 ሰው ይሞታል፡፡ ይህ ማለት በየሰዓቱ 190፣ በየደቂቃው ደግሞ 30 ሰው ይሞታል ማለት ነው፡፡

በጉባዔው ላይ ከአዲስ አበባ ጎዳናዎች በአንዱ ላይ በመኪና አደጋ ምክንያት ልጃቸውን ያጡ ሚስ ቪታሊ የተባሉ አንዲት ኢጣልያዊት የእማኝነት ቃል አሰምተዋል፡፡

የመለስካቸው አምኃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG