በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር እራሱን ከምርጫዉ አገለለ


ድርጅቱ ውሳኔውን ያሳለፈው ለሰላም ሲል መሆኑን ገልጿል

የአፋር አብዮታዊ ደሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር (አርዱፍ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ መሃመድ አወል ጉግርሽ በክልሉ ተፈጽሟል ያሉትን ግድፍቶች ሲዘርዝሩ፣ ሕዝቡ እንዳይመዘገብ ይከለከላል፣ የምርጫ ካርድ የመንግስት ታማኝ ካልሆኑ በስተቀር አይሰጥም ብለዋል።

አቶ መሃመድ ይህ አስራር ባለፍት ምርጫዎችም የነበሩና በወቅቱ ያሰሙት ተቃውሞ ሰሚ እንዳላገኘ ይናገራሉ። አሁንም ይህ ምርጫ ከመነሻው የተበላሸ መሆኑን ለምርጫ ቦርድ ሁለት ሶስቴ በደብዳቤ ገልጾ ምንም መልስ አላገኘንም ብለዋል።

ስለሆነም በምርጫ ወቅት ሊቀሰቀስ የሚችል ሁከትን ለማስቀረት ሲል አርዱፍ እራሱን አግልሏል ብለዋል።

የአፋር አብዮታዊ ደሞክራሲያዊ አንድነት ግንባር የምርጫ ስነ ምግባሩን ከፈረሙ 60 ፓርቲዎች አንዱ ነው።

XS
SM
MD
LG