በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የአባላቶቻችን እሥር ሊካሄድ በታቀደው ድርድር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራል" - መኢአድ


መኢአድ
መኢአድ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የማዕከላዊ ምክር ቤት አባልና የሰሜን ጎንደር ሰብሳቢ ከየካቲት 7 ቀን ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኙ ፓርቲው አስታወቀ፡፡

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የማዕከላዊ ምክር ቤት አባልና የሰሜን ጎንደር ሰብሳቢ ከየካቲት 7 ቀን ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኙ ፓርቲው አስታወቀ፡፡ አባሎቻችን እየታሠሩ ያሉበት ሁኔታ ሊካሄድ በታቀደው ድርድር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሣድር ይችላል ብለዋል - የፓርቲው ዋና ፀኃፊ አቶ አዳነ ጥላሁን፡፡

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ዛሬ እንዳስታወቀው የማዕከላዊ ምክር ቤት አባልና የሰሜን ጎንደር ዞን ሰብሳቢ የሆኑት ሻምበል ንጉሴ ደርሶ ለአለፉት ሁለት ሣምንታት በእስር ላይ ናቸው፡፡

የፓርቲው ዋና ፀኃፊ አቶ አዳነ ጥላሁን ለአሜሪካ ድምፅ እንዳስረዱት ከፍተኛ አመራሩ የታሠሩት ጭልጋ ወረዳ ወደ ምትገኝ "ጉባዔ" በተባለች ቀበሌ ልጆቻቸውን ለመጠየቅ እንደሄዱ ነው፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

"የአባላቶቻችን እሥር ሊካሄድ በታቀደው ድርድር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራል" - መኢአድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:08 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG