በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ታሞ መሞቱን ነገሩኝ፤አስክሬኑን ተቀብዬ ቀበርኩ” - የሟች አባት


አዲግራት ዩኒቨርስቲ አርማ
አዲግራት ዩኒቨርስቲ አርማ

በአዲግራት ዩኒቨርስቲ ጥር 17 ለሊት ለጥር 18/2009 አጥቢያ ሕይወቱ ያለፈው የአንደኛ ዓመት ተማሪ ሹሚ አስክሬን ለቤተሰቦቹ ሲሰጥ ታማሚ እንደነበር እንደተነገራቸው ወላጅ አባቱ ገልፀው “ልጄ ከሦስት ወር በፊት ከእኔ ጋር ሲሄድ ጤነኛ ነበር” ብለዋል።

በዩኒቨርስቲው የውሃ አቅርቦት መጓደልን ተከትሎ ተማሪዎች ተቃውሞ ማካሄዳቸውን፣ በዚህም ምንም የታሰረ ተማሪ እንደሌለ፣ የሞተው ተማሪም ከዚህ ተቃውሞ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለውና በሕመም መሞቱን የዩኒቨርስቲው የተማሪዎች ሕብረት ፕሬዝዳት ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ በወቅቱ ተናግራለች።

የዝግጅት ክፍላችን የሟችን አባት አፈላልጎ አግኝቷል። አባት ልጃቸው ታሞ እንደማያውቅ ሲናገሩ፤ ሟችን በቅርበት የሚያውቅ ተማሪ፤ ሕመም እንዳልነበረበት ተናግሯል።

ሹሚ ለማ በቀለ የአዲግራት ዩኒቨርስቲ የባዮ ቴክኖሎጂ የአንደኛ ዓመት ተማሪ ነው። ስሙን እና ማነነቱ እንዲገለጽ ያልፈለገው በዚሁ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆነና ለሟች ቅርበት እንዳለው የሚናገረው ሌላ ተማሪ ፤ ተማሪ ሹሚ ጥር 17/2009 እስከ እኩለ ለሊት ድረስ ቤተ መጽሐፍት ውስጥ ሲያጠና ቆይቶ ወደ መኝታ ክፍሉ እንደገባ ይናገራል።

“ጠዋት አስክሬኑ ተገኘ አሉ። ነገር ግን ለሊት ሰባት ሰዓት ላይ መሞቱን መኝታ ክፍሉ ውስጥ የነበሩት ሲናገሩ ነበር። የመሞቱን ምክኒያት ­ለእናንተው ለአሜሪካ ድምጽ የተናገሩት ደግሞ ሲታመም እንደነበር ገልፀዋል። እንደዚህ በአንዴ የሚገድል በሽታ እንዳለው መረጃ የለኝም። እርሱ ላይም አይቼ አላውቅም።” ብሏል።

የሟቹን ተማሪ ሹሚ ለማን ወላጅ አባት አነጋግረናቸው ነበር። አቶ ለማ በቀለ ሰንዳፋ አካባቢ ነዋሪ ናቸው። ተደውሎ የልጃቸው አስከሬን ወደ እርሳቸው እየመጣ እንደሆን እስኪነገራቸው ድረስ ልጃቸው ስለመሞቱ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።

“ ያው ታሞ ሞተ አሉኝ። ልጄ ከእኛ ዘንድ እስኪሄድ ድረስ ጤነኛ ነበር። ወደ ዩኒቨርስቲው ከሄደ ገና ሦስት ወሩ ነው። የአንደኛ አመት ተማሪ ነው። ከሄደም በኋላ ስለመታመሙ አልተነገረኝም።”

አቶ ለማ የልጃቸውን አስክሬን ማየት እንደሚፈልጉ ጠይቀው፤ ልጃቸው ታሞ መሞቱን ሆስፒታል ተወስዶ መመርመሩን ገልጸው እንደነገሯቸው ይናገራሉ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

“ታሞ መሞቱን ነገሩኝ፤አስክሬኑን ተቀብዬ ቀበርኩ” - የሟች አባት
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:35 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG