በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

​​የኢትዮጵያ መንግሥት ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን ከእስር እንዲለቅ ዩናይትድ ስቴትስ ጥሪ አቀረበች

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እ.አ.አ. ሰኔ 19, 2011 በመንግስት ባለሥልጣናት ታሰረ
ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እ.አ.አ. ሰኔ 19, 2011 በመንግስት ባለሥልጣናት ታሰረ

ውብሸት አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ዩኒቲ ኮሌጅ ነው የጋዜጠኝነት ሞያውን የጀመረው። ከዚያም አሁን በታገደው ሃዳር በተባለ ነፃ ሳምንታዊ ጋዜጣ ሞያውን ቀጠለ። እ.አ.አ. ጥር 19, 2012 በአዲስ አበባ የሚገኝ ፍርድ ቤት በአሸባሪነትና እና ለአሸባሪነት ገንዘብ በመከፈል ወንጀለኛ ተባለ።

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እ.አ.አ. ሰኔ 19, 2011 በመንግስት ባለሥልጣናት ታሰረ። ውብሸት በአማርኛ ቋንቋ የሚሰራጨው የአውራምባው ታይምስ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነበር።

አንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት እንደገለጸው ውብሸት ከመታሰሩ በፊት ገዢው ፓርቲ የሚተች ጽሁፍ አቅርቦ ነበር።

ውብሸት አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ዩኒቲ ኮሌጅ ነው የጋዜጠኝነት ሞያውን የጀመረው። ከዚያም አሁን በታገደው ሃዳር በተባለ ነፃ ሳምንታዊ ጋዜጣ ሞያውን ቀጠለ። እ.አ.አ. ጥር 19, 2012 በአዲስ አበባ የሚገኝ ፍርድ ቤት በአሸባሪነትና እና ለአሸባሪነት ገንዘብ በመከፈል ወንጀለኛ ተባለ።

ከዚያም 14 አመታት እስራት ተፈርዶበት በአሁኑ ወቅት በዝዋይ ማረምያ ቤት ይገኛል። የጤንነቱ ጉዳይም አስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛል። የኢትዮጵያ መንግስት ውብሸት ታዬን እንዲለቅ እንጠይቃለን።

የሽብር ህጉም በነጻ ሃሳብን ለመግለጽ እንቅፋት እንዳይሆና የጋዜጠኞችን ስራ ለማጣጣል መንግስቱ እንዳይጠቀምበት ጥሪ እናቀርባለን።

XS
SM
MD
LG