በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በጋዜጦች


ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ የኩላሊት ነቅሎ ተከላ ህክምና ተደረገ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ከ 200 በላይ የሚሆኑ ህገ-ወጥ ሰው አሸጋጋሪዎችን ማሰሩ ገለጸና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አፍሪቃን ላገኘቻቸው ስኬቶች አሞገሰ የሚሉትን ርእሶች ነው በዛሬው አፍሪቃ ነክ ርእሶች ዝግጅታችን የምንመለከተው።

ኢትዮጵያ ውስጥ በሚችጋን ዩኒቨርሲቲ የተመራ የህክምና ቡድን ባለፈው ሳምንት በሀገሪቱ ለመጀመርያ ጊዜ የኩላሊት ነቅሎ ተከላ ህክምና ማድረጉን News Medical የተባለ በአለም ደረጃ ስለተከሰቱት የህክምና ግኝቶችና ጥናቶች የሚዘግብ ድረ-ገጽ ጠቁሟል። የህክምናው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ የኩላሊት ነቅሎ ተከላ ህክምና ማዕከል ለመክፈት ከሁለት አመታት በላይ እንደቆየ ጽረ-ገጹ ጨምሮ ገልጿል።

በቀዶ ህክምና ሀኪም ዶክተር Jeffrey D. Punch የተመራው ቡድን አዲስ አበባ በሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሚለንየም ህክምና ኮሌጅ ሶስት የኩላሊት ነቅሎ ተከላ ህክምና አድርገዋል። ኩላሊቶቹ የተገኙት በህይወት ካሉ ለጋሾች ሲሆን ኩላሊቶች የተተከሉላቸው በሽተኞችም ሆኑ ኩላሊት የለገሱት ሰዎች ሁሉ በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኙ ድረ-ገጹ ላይ የወጣው ዘገባ ጠቅሷል።

BBC የብሪታንያ የዜና ስርጭት ኮርፕረሽን ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት በያዝነው አመት ከ 200 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ህገ-ወጥ በሆን መንገድ የሚያሸጋግሩ ሰዎችን እንደያዘ ዘግቧል። ሰዎች እንዲህ አይነቱን አስከፊ ጉዞ እንዳያደርጉ ለማሳመንም ስፊ ቅስቀሳ እየተካሄደ መሆኑን አክሏል።

መንግስት ስደትን ለመገደብ እርምጃ ለመውሰድ የተገደደው 30 ኢትዮውያን ባለፈው ሚያዝያ ወር እስላምዊ መንግስት ነኝ በሚለው ቡድን በአሰቃቂ ሁኔታ ከተገደሉ በኋላ መሆኑን የ BBC ድረ-ገጽ ላይ የወጣው ጽሁፍ ያወሳል።

ከ 100 በላይ የሚሆኑ ህገ-ወጥ አሽጋጋሪዎች ከሱድን ጋር በምትዋሰነው መተማ ከተማ እንደተያዙና በአንድ ወቅት በቀን ከ 250 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በመተማ በኩል ወደ ሱዳን ይወጡ እንደነበር ዘገባው ጠቁሟል።

አፍሪቃ በትምህርትና የልጆች ሞትን በመቀነስ ረገድ ላሳየችው ጉልህ መሻሻል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደተሞጎሰች የጋርዲያን ጋዜጣ ድረ-ገጽ ጠቁሟል። በሚለንየም የልማት ግብ ላይ የቀረበ ዘገባ አፍሪቃ የአዲሱን የልማት ግብ ለማሳካት የአፍሪቃ መሪዎች ያገኙትን ስኬት ማጠናከር አዲስ የገንዘብ ምንጭንም መፈለግ ይኖርባቸዋል ይላል ድረ-ገጹ ላይ የወጣው ዘገባ።

የአፍሪቃ ሃገሮች የሚለንያም ልማት ግበን በተግባር ላይ በማዋል በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚገቡት ልጆች ብዛትን ከፍ በማድረግ የሴቶች የፖለቲካ ውክልናን በማበራከት የልጆችንና የእናቶች ሞትን በመቀነስ የ HIV መስፋፍትን በመገደብ አመርቂ ውጤት እንዳሳዩ አዲሱ ዘገባ መግለጹን ጋርድያን ድረ-ገጽ ጠቅሷል።

ሙሉውን ቅንብር ያድምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:08:42 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG