በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በጋዜጦች


አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ /ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/
አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ /ፎቶ ከኢንተርኔት የተገኘ/

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሞት ላይቀጡ እንደሚችሉ ተገለጸ፣ የሱዳኑ ፕረዚዳንትና አለም አቀፍ የወንጀል ችሎት የሚሉት ርእሶች ባዛሬው "አፍሮቃ በጋዜጦች" ዝግጅታችን ይቅርባሉ።

The Guardian Nigeria የተባለ ድረ ገጽ በዘገበው መሰረት የብሪታንያ ዜጋ የሆኑት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ምህረት አይደረግላቸውም። ነገር ግን በሞት ላይቀጡ ይችላሉ ሲል የኢትዮጵያ መንግስት ተናግሯል።

60 አመት እድሜ የሆናቸው የግንቦት ሰባት መሪ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከ 6 አመታት በፊት በአሸባሪነት ክስ በሌሉበት ሞት ተፈርዶባቸው ነበር። ከአንድ አመት በፊት ደግሞ በየመን ተይዘው ለኢትዮጵያ ስለተሰጡ ታስረዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ቃል-አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል “የኢትዮጵያ ፈርድ ቤት የሞት ቅጣት አያዘወትርም። የተበየነበት ቅጣት ወደ እድሜ ይፍታህ ሊለወጥ ይችላል። ምህረት ግን አይደረገለትም ሲሉ ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ የዜና አገልግሎት መናገራቸውን፣ The Guardian Nigeria ድረ ገጽ ጠቅሷል።

ሊታረም የማይችል፣ መንግስትን ለመግልበጥ የሞከረ፣ ቦምቦችን የቀበረ፣ እአአ በ 2005 አም ምርጫ ከተካሄደ በኋላ መነሳሳትን ያደራጀ ሰው ነው ሲሉም አቶ ሽመልስ ከማል መናገራቸውን The Guardian Nigeria ድረ ገጽ አውስተዋል።

የዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ድረ-ገጽ በበኩሉ ብዛት ያላቸው የአፍሪቃ መሪዎች አለም አቀፍ የወንጀል ችሎትን የሚጠሉበትን ምክንያት ለመተንተን ይሞክራል። ዋናው መሰረቱ ሄግ የሆነው አለም አቀፍ የወንጀል ችሎት እአአ በ 2002 አም (ከ አስራ ሶስት አመታት በፊት ማለት ነው) የተመሰረተው፣ ለበጎ አላም እንደነበር አያጠራጥርም። ሀገራት ሊያከናውኑት ያልቻሉትን ወይም ያልፈለጉትን ወንጀል መርምሮ ለፍርድ ለማቅረብ ነብር የተመሰረተው። በተግባር ላይ የማዋሉ ጉዳይ ግን ከባድ ሆኗል ይላል ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ድረ-ገጽ ላይ የወጣው ጽሁፍ። ዝርዝር ዝግጅቱን ያድምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:08:35 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG