በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ በጋዜጦች


አምባሣደር ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
አምባሣደር ዲና ሙፍቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ
የኢትዮጵያ መንግስት ሱዳንና ደቡብ ሱዳን የኔ ነው በሚሉት አብየ ክልል አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደርና አንድ የጎሳ መሪ መገደላቸውን ባለፈው ማክሰኞ እንዳወገዘ ሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ዘግቧል።

ኢትዮጵያዊው ሰላም ጠባቂ ወታደርና የንጎክ ዲንቃ ጎሳ መሪ Kuol Deng Kuol ባለፈው ቅዳሜ የተገድሉት በአብየ በተመደበው የተባበሩት መንግስታት ጊዚያዊ ሃይል ታጅቦ ይጓዝ የነበረው ካምዮን ሚሰርያ በተባሉት አርብቶ አደር የአረብ ጎሳዎች አድፍጠው ባጠቁት ወቅት እንደሆነ ጋዜጣው ጠቅሷል።

“የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ ሰላም ጣባቂዎች ላይ ያነጣጠረው
ግድያንና ጥቃትን አጥብቆ ያወግዛል" ሲሉ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስገንዝበዋል" ይላል ሱዳን ትሪቡን ጋዜጣ ።

cbsnews የተባለው የአሜሪካ ቴሌቪዥን ድረ-ገጽ በዘገበው መሰረት ደግሞ ኢትዮጵያ 787 ድሪምሊነር የተባሉት ዘመናዊ አይሮፕላኖችዋ እንዳይበሩ ታግደው ለነበሩበት ጊዜ ከቦይንግ ካሳ ትጠይቃለች።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም እስካሁን ባለው ጊዜ አየር መንገዱ አይሮፕላኖቹ ወደ በረራ እንዲመለሱ በማድረግ ጉዳይ ላይ አትኩሮ እንደነበር ገልጸው የኩባንያው ቀጣይ ስራ ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ስለ ካሳ ጉዳይ መነጋገር መጀመር ነው በማለት ለአሶሼትድ ፕረስ የዜና አገልግሎት እንደታናገሩ cbsnews ድረ-ገጽ ጠቅሷል። ሌሎች ዘባዎችንም አካተናል።
AMH-af-Ethiopia-Press-Review-5-10-13
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:26 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG