በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አለም አቀፍ የቀውስ አስወጋጅ ቡድን ዘገባ የኤርትራ ሁኔታ እንደሚያሳስብ ገለጸ


International Crisis Group ማለት አለም አቀፍ የቀውስ አስወጋጅ የተባለው ቡድን ያወጣው ዘገባ በኤርትራ እየጎላ የሄደው ያለመረጋጋት ሁኔታ እየተገለለች የሄደችውን አነስተኛ ሀገር በውስጣዊ ትርምስ ውስጥ ሊከት ይችላል ይላል። ለሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የሚያመች ስርአት ባለመኖሩም ወታደራዊው ሀይል የመሪነት ሚና ሊጫወት እንደሚችል አዲሱ ዘገባ ገልጿል።

ባለፈው አመት የኢትዮጵያ ወታደሮች ሁለት ጊዜ ወደ ኤርትራ ለመግባት መቻላቸውና በያዝነው አመት ቀደም ሲል በሁኔታዎች ያልረኩ ወታደሮች ለማመጽ መሞከራቸው ራሱ የኤርትራ ወታደራዊ ሃይል ያለበትን “ደካማ ሁኔታን” ሊያጋልጥ ችሏል ሲሉ የአለም አቀፉ ቀውስ አስወጋጅ ቡድን የአፍሪቃ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ Cedric Barnes ተናግረዋል።

የኤርትራው ፕረዚዳንት የፖለቲካ አማካሪ አቶ የማነ-ገብረአብ በበኩላቸው የዘገባው አባባል ከእውነታው ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ብለዋል።
ለአራት አመታት በተከታታይ በአከባቢው ኢኮኖሚያቸው እጅግ እያደገ በመሄድ ላይ ካሉት ሀገሮች መከካል እንፈረጃለን። በማህበረሰባዊ ዘርፍም የሚደነቅ ስኬት አግኝተናል። ሀገሪቱም የተረጋጋች ነች ብለዋል።
AMH-ph-af-ICG-Eritrea-3-29-13
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:13 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG