በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰላም እሸቱ እና ሙሉጌታ ይህደጎ በጉዲፈቻ የወሰዷቸውን ጨምሮ የሰባት ልጆች ወላጆች - “ይቻላል” ይላሉ


ሰላምና ሙሉጌታ
ሰላምና ሙሉጌታ
ሶፊያ አለማየሁ


የግል ህይወት ለማሸነፍ በምንጣጣርበት በዚህ የውድድር ዘመን አንዳንድ ሰዎች ከራሣቸው አልፈው፤ ካላቸው አካፍለው ለሌሎች ህይወት እና ተስፋ፣ ለብዙኃን ተምሣሌት ይሆናሉ፡፡

ወጣት ሠላም እሸቱ እና ሙሉጌታ ይህደጎ ከነዚህ ግብረ ሠናይ ሰዎች መሀል ናቸው፡፡ ሰባት ልጆች አሏቸው፡፡ ከነዚህም አምስቱ በጉዲፈቻ የወሰዷቸው ናቸው፡፡ ከዓመት በፊት፣ ወደ ካሊፎርንያ ከመምጣታቸው በፊት የሚኖሩት አምስት ልጆቻቸውን ባገኙበት በኢትዮጵያ፣ ናዝሬት ከተማ ነበር፡፡

“ሠላም ገና እጮኛዬ ሆና ለመጋባት ያስቀመጠችልኝ ቅድመ ሁኔታ፤ 'ከተጋባን ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆችን እንረዳለን፤ ድጋፍህ እንደማይለየኝ ቃል ግባልኝ’ የሚል ነበር” ይላል ሙሉጌታ፡፡ ጥያቄዋን በእሺታ የተቀበለው ሙሉጌታ ‘ወደፊት ትተወዋለች’ የሚል ግምት እንደነበረው ይናገራል፤ ነገር ግን ሠላም ይህንን ዓላማዋን አልረሣችውም፡፡

የመጀመሪያ ልጃቸውን ታከለ የተዋወቁት ከዘጠኝ ዓመት በፊት ነበር፡፡ ታሪኩ በወቅቱ የስድስት ዓመት ልጅ ነበር፡፡ ሁለቱንም ወላጆቹን አጥቶ ከ75 ዓመት አያቱ ጋር ይኖራል፡፡ ስለ ሁኔታው ሙሉጌታ ሲያስረዳ “የመጀመሪያ ልጃችንን ያገኘነው ልብ በሚሰብር ሁኔታ ነበር” ይላል፡፡

ሰላም እሸቱ እና ሙሉጌታ ይህደጎ ከሰባቱ ለጆቻቸው ጋር
ሰላም እሸቱ እና ሙሉጌታ ይህደጎ ከሰባቱ ለጆቻቸው ጋር


ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆች በየቀኑ የሚያሣልፉትን ሥቃይና መከራ በቅርብ መከታተል የጀመሩት እነዚህ ቤተሰቦች መጀመሪያ ላለመውለድ ተስማምተው ነበር፡፡ በጉዲፈቻ የወሰዷቸው ልጆቻቸው የወለዷቸው እስኪመስሏቸው ድረስ ጠብቀው በሦስተኛ ዓመታቸው አንድ ልጅ ወለዱ፡፡

“ሂደቱ አንዳንዴ ከባድ የነበረ ቢሆንም በውስጤ ግን ቀልሎኝ ነው ያሣለፍኩት፤ አንድም ቀን ተቆጭተን አናውቅም” የምትለው ሠላም ልጅን በጉዲፈቻ ስለማግኘት ስትናገር በተለምዶ ‘ከአብራክ ያልወጣ ልጅ የራስ አይሆንም’ የሚለው አባባል ከእውነት የራቀ ነው ትላለች፡፡ ሠላም “… ያ በተወለደ ልጅና ወላጅ መካከል ያለው ተፈጥሯዊ ፍቅር እና ትስስር ከጉዲፈቻ ልጅም ጋር በትዕግስት በእርግጠኝነት ይገኛል” ትላለች፡፡

በአዘአ በ2007 ዓ.ም በወጣው የተባበሩት መንግሥታት ለሕፃናት ደራሽ ድርጅት - ዩኒሴፍ (UNICEF) መረጃ መሠረት በኢትዮጵያ 4.6 ሚሊዮን አካባቢ የሚሆኑ ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናት አሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ልጆች ወላጆቻቸውን በኤድስ ምክንያት ያጡ ናቸው፡፡

ታድያ ሳይጠይቁ ወደዚህ ዓለም ያመጣናቸውን እነዚህን የነገ ተረካቢዎች ከዚህ አደገኛ ህይወት ለማውጣት ከምንጠቀምባቸው መፍትሔዎች አንዱ ልጆችን በጉዲፈቻ ማሳደግ አንዱ መንገድ እንደሆነ ይታመናል፡፡

ዓለምአቀፍ ወይም ሃገር አቋራጭ ጉዲፈቻ የመጨረሻ አማራጭ እንዲሆን የምናደርገው ጥረት ለማገዝ ደግሞ የሀገር ውስጥ ጉዲፈቻን ማበረታታት ከቀዳሚዎቹ ትኩረቶቻችን መካከል ሊሰለፍ ይገባዋል፡፡ ለዚህም ነው የእነዚህ ወጣቶች ታሪክ የሌሎችን ህይወት ከመቀየር በተጨማሪ የነገን ኢትዮጵያ ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያለው፡፡
ታከለ እና መኩ የመጀመሪያና ሁለተኛ ልጆች
ታከለ እና መኩ የመጀመሪያና ሁለተኛ ልጆች



ሠላምና ሙሉጌታ በበጎነት እና በድፍረት ስለመረጡት የህይወት ጉዞ፤ ስላለፉት ፈተና እና ተስፋቸው በፕሮራማችን ባደረግንላቸው ቃለ ምልልስ አካፍለውናል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:13:34 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

please wait

No media source currently available

0:00 0:09:01 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG