በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮ-ጀርመን ግንኙነትና የመብቶች ጉዳይ


የጀርመኑ እንደራሴ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን አላመኑም

በጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስትር ሚስተር ዲርክ ኒበል የተመራ አንድ የጀርመን መንግሥት ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት አድርጎ መመለሱ ይታወሳል፡፡

ያንን ጉብኝት ተከትሎ የሃገሪቱ ፓርላማ የእርዳታና የኢኮኖሚ ትብብር ኮሚቴ ባለፈው ሣምንት ውስጥ በርሊን ላይ ገለፃዎችን አዳምጦ ነበር፡፡

ከገለፃዎቹ በኋላም ተከታይ የውይይት ምሽት ተካሂዷል፡፡

የጀርመኑ ቡንደስታግ (ፓርላማ) አባልና የእርዳታና የኢኮኖሚ ትብብር ኮሚቴው ምክትል ሊቀመንበር ሚስተር ቲሎ ሆፐ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዞ የነበረው የጀርመን መንግሥት ልዑካን ቡድን አባል ሆነው ሄደዋል፡፡

ባለፈው ሣምንት የተካሄደውንም የኮሚቴውን የኢትዮጵያ ጉዳይ ማብራሪያ ስብሰባ መርተዋል፡፡

የእንደራሴው ቲሎ ሆፐ ፅ/ቤት ትናንት አንድ የፕሬስ መግለጫ አውጥቶ በትኗል፡፡ መግለጫው በመግቢያው ላይ ባሉ ሁለት መሥመሮች እንዲህ ይላል፡- "የዴሞክራሲን እጦትና የሰብዓዊ መብቶችን መረገጥ ክእንግዲህ ለማስተናገድ የማይሹቱ ድምፆች ይበልጥ እያስተጋቡ የሄዱት በዐረቡ ዓለም ብቻ አይደለም፤ ይህ ሁኔታ በኢትዮጵያም እየተከሰተ ነው፡፡"

የቡንደስታጉ የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ መሪዎችና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ጋር ተገናኝቶ መነጋገሩን የእንደራሴ ቲሎ ሆፐ ፅ/ቤት መግለጫ አመልክቶ ኮሚቴው ያነጋገራቸው የፖለቲካ ሰዎችና የመብቶች ተሟጋቾች አዲስ አበባ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄድ መከልከሉን፣ ሥርዓቱን የሚተቹ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞችና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተጠሪዎች እንደሚታሠሩ ያስረዱ መሆኑን ገልጿል፡፡

የጀርመን መንግሥትም ከኢትዮጵያ ጋር ወደኢኮኖሚ ልማት ትብብር ድርድሮች ሲገባ እነዚህን አሣሣቢ ያሏቸውን የሰብዓዊ መብቶች ረገጣ ጉዳዮችን ግምት ውስጥ እንዲያስገባ የሚስተር ቲሎ ሆፐ ፅ/ቤት የፕሬስ መግለጫ ያሣስባል፡፡

እንደራሴ ቲሎ ሆፐ በጀርመን የተቃዋሚው አረንጓዴ ፓርቲ አባልም ናቸው፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG